Skip to content

invitation to bids by ethiopian defence ministry

    የጨረታ ማስታወቂያ

    የጨረታ መስያ ቁጥር CON/TRS/ANNUAL PROCUREMENT 02/2016

    በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት የተለያዩ የጫማ ማስቀመጫ ቤትና የውኃ ቤት በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል::

    በዚህ መሰረት:

    1 በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት የጫማ ማስቀመጫ ቤትና የውኃ ቤት ግንባታዎች፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ኮንትራክተሮች

    1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
    2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (Valve added tax) ተመዝጋቢ የሆኑ
    3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
    4. በኮንስትራክሽን ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ያላቸው
    5. በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ እና በመንግስት የኮንስትራክሽን ስራ የግልፅ ጨረታ አፈፃፀም መመሪያ መስፈርት መሠረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ
    • በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ WC /GC ደረጃቸው 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑና አምስት ዓመት ተከታታይ የሠሩትን የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በየትኛውም የመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይ ፕሮጀከት ህጋዊ ውል ገብተው ስራውን ያለምንም የጥራት ጉድለት ያጠናቀቀበትን የምስክር ወረቀት(የስራ ልምድ) ማቅረብ የሚችል፣
    • ከ2008 ዓ/ም ጀምረው ባለው ጊዜ ውስጥ በተመሳሳይ ስራ አሸንፈው ያጠናቀቁት ፕሮጀከት በዝርዝርና ከነመልካም ስራ አፈፃፀም ሰርተፍኬታቸው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
    • የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን /ቴክኒክ ብቃት መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና ኦርጅናል(ኮፒ ሲጠየቁ አቅርቦ ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
    • ማንኛውንም ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲሞሉ ከ.ተ.እ.ታ በፊት ያለ የነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል::
    • ቴክኒካል ውድድሩን ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሽያሉ ሠነድ አይከፈትም::
    • የጨረታ ማስከበሪያ unconditional Bank Guarantee ወይም የክፍያ ማዘዣCPO 120,00.00 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማና ማህተም መደረግ አለበት::
    • ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉ እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ካሟሉ በኋላ የግንባታ መሣሪያዎቻቸውን በቦታው አጓጉዘው ማድረስ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
    • ተጫራቾች ማጭበርበር፣ ሙስና እና ማታለልን በተመለከተ ላለመፈፀም በኢትዮጵያ ህጐች የተደነገገውን የሚያከብር እና የሚያስከብር መሆን አለበት
    • የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
    • አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት በኋላ ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፋበት ዋጋ 10% conditional Bank Guarantee ወይም (CPO) አሰርተው ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
    • ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞሉ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
    • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል፣ ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይቻልም
    • ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ማስረጃ (ዋጋ ላይ) ስርዝ ድልዝ (ፍሉድ) ካለበት ከጨረታ ውጪ
      ይሆናል::
    • ለጨረታ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ9ዐ ቀናት የማይቀየር (የፀና) ይሆናል::
    • ማንኛውንም ለግንባታው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና አጠቃላይ ወጪዎችን በአሸናፊው ተቋራጭ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡

      ጨረታ የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ቀን፡
    • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጥር 23/2016 ዓ/ም 8፡15 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሁርሶ በሚገኘው በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንትጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለዚሁ ጨረታ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ –
    • በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 054050
    • በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ግዥ ዴስክ ስልክ ቁጥር 0254470115 የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል የከፈሉበትን ህጋዊ ደረሰኝ በማሳየት ሀርድ ኮፒ መውሰድ ይችላሉ፡
    • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

      ተጨማሪ መረጃ ስስክ ቁፕር፡-0254470115
      ሁርሶ
      በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰላም ማስከበር ማዕከል
      የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት

    Read more Construction Tenders

    https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-tenders

    http://constructionproxy.com/category/tender