Skip to content

የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች ፦

  የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች ፦

  ” … በ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሆነ በማኑዋል ዕጣ የማውጣት ሂደቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሊወጣለት ከሚገባው ባለእድለኛ ወጪ ለሌላ ለማይመለከተው አካል እንዳይተላለፉ የሄደበትን ርቀት እናደንቃለን፡፡

  ነገር ግን ይህ ቁርጠኝነት በባለ3 መኝታ 2005 ዓ.ም የ20/80 ተመዝቢዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲገለጽ እንፈልጋለን፡፡

  በቅርቡ የተሰረዘውን የ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓትን አስመልክቶ በዋዜማውና ከዛ በኋላ በተሰጡ መግለጫዎች ባለ3 መኝታ የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ውስጥ እንደማይገባ የተሰጠው መግለጫ ግልጽነት የጎደለውና ማብራሪያ የሚሻ ሆኖ አግኝተነዋል።

  ይህ ሁኔታ የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎችን በእጅጉ ያሳዘነ፣ ያስደነገጠና ግራ ያጋባ ሆኗል፡፡

  ይህን አስመልክቶ በከተማ አሰተዳደሩ የተለያየ የስራ ኃላፊዎች በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ ሚዲያዎች በሚሰጡት መግለጫዎችና ማብራሪያዎች ላይ የ20/80 ባለ3 መኝታ የ2005 ተመዝቢዎችን አቤቱታና ቅሬታዎችን በግልጽ ከመመለስ ይልቅ ሆን ተብሎ በሚመስል መልኩ ቸል በማለትና በማድበሰበሰ እየታለፈ በመሆኑ በመንግሥት ላይ ያለንን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል። “

  የ2005 የ20/80 ባለሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች አሉን ያሏቸውን ጥያቄዎች በዝርዝር በመፃፍ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

  (ሙሉ ጥያቄያቸው በዝርዝር ተገልጿል)

  photo_2022-07-27_17-59-16.jpg
  photo_2022-07-27_17-59-17 (2).jpg
  photo_2022-07-27_17-59-17.jpg
  photo_2022-07-27_17-59-17 (2).jpg

  Read more Articles

  https://constructionproxy.com/ethiopian-construction-update-and-articles

  https://constructioninethiopia.com/category/articles/